ዘፍጥረት 30:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “እነሆ፤ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፤ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከርሷ ጋራ ተኛ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ባርያዬ ባላ እነሆ አለች፥ ድረስባት፥ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርሷም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “እነሆ፥ አገልጋዬ ባላ እዚህ አለች፤ በእኔ ምትክ ልጅ እንድትወልድልኝ ወደ እርስዋ ግባ፤ በዚህ ዐይነት በእርስዋ አማካይነት የልጆች እናት እሆናለሁ” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ወደ እርስዋ ግባ፤ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፤ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋምም ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች፤ ድረስባት፤ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች። |
ከዚያም ሽማግሌዎቹና በከተማዪቱ በር አደባባይ የነበሩት ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “እኛ ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት፣ የእስራኤልን ቤት በአንድነት እንደ ሠሩ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፤ አንተም በኤፍራታ የበረታህ ሁን፤ ስምህም በቤተ ልሔም የተጠራ ይሁን።