ዘፍጥረት 2:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፥ ሉልና የከበረም ድንጋይ በዚያ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚያ አገር ወርቅ ንጹሕ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ውድ የሆነ ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ይገኛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኚል። |
በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ፣ በዔድን ነበርህ፤ እያንዳንዱ የከበረ ድንጋይ አስጊጦህ ነበር፤ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮን፣ አልማዝ፣ መረግድ፣ ኢያሰጲድ፣ ሰንፔር፣ በሉር፣ ቢረሌና የከበረ ዕንቍ። ልብስህም የሚያብረቀርቅ ዕንቍ ወርቅ ነበር፤ የተዘጋጁትም አንተ በተፈጠርህበት ዕለት ነበር።