ዘፍጥረት 18:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ “በሰዶም ከተማ ዐምሳ ጻድቃን ባገኝ ለእነርሱ ስል አገሪቱን በሞላ እምራለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም፦ “በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “በሰዶም ከተማ ውስጥ በደል ያልሠሩ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ባገኝ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን ፈጽሞ አላጠፋም” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “በሰዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ከተማውን ሁሉ ስለ እነርሱ አድናለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፤ በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምስ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ። |
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በወይኑ ዘለላ ውስጥ ጭማቂው ገና እንዳለ ሁሉ፣ ሰዎችም፣ ‘በውስጡ በረከት ስላለ አትቍረጡት’ እንደሚሉ፣ እኔም ስለ ባሮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።
“በኢየሩሳሌም መንገዶች እስኪ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደ ታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህችን ከተማ እምራታለሁ።