ዘፍጥረት 17:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋራ መነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግግሩንም ከእርሱ ጋር በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ተለይቶ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አብርሃምን ካነጋገረው በኋላ ከእርሱ ተለይቶ ወደ ላይ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ንግግሩን ከእርሱ ጋር በፈጸመ ጊዜ ከአብርሃም ተለይቶ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግግሩንም ከእርሱ ጋር በፈጸም ጊዜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ተለይቶ ወጣ። |
ይኸውም የእሳቱ ነበልባል ከመሠዊያው ወደ ሰማይ ሲወጣ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በነበልባሉ ውስጥ ዐረገ። ማኑሄና ሚስቱ ይህን ሲመለከቱ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።