ዘፍጥረት 10:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኵሽ የናምሩድን አባት ነበረ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኩሽም ናምሩድን ወለደ፥ እርሱም በምድር ላይ ቀዳሚው ኃያል ጦረኛ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኩሽ በዓለም ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረውን ናምሩድን ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኀያል መሆን ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሽም ናምሩድን ወለደ እርሱም በምድር ላይ ኃያክክ መሆንን ጀመረ። |
ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት። እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ረዣዥምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!
የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤ አሦራዊው ምድራችንን ሲወርር፣ ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣ እርሱ ነጻ ያወጣናል።