ዘፍጥረት 10:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኵሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆች፦ ሳባ፣ ድዳን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሳብታ፥ ራዕማ እና ሳብተካ ናቸው። የራማ ልጆች፥ ሳባ እና ደዳን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፥ ሐዊላ፥ ሳብታ፥ ራዕማና ሳብተካ ናቸው። የራማ ልጆች፥ ሳባና ደዳን ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ሬጌም፥ ሰበቅታ ናቸው። የሬጌም ልጆችም ሳባ፥ ዮድዳን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኩሽም ልጆች ሳባ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። |
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።
“ ‘የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋራ ይገበያዩ ነበር፤ ምርጥ የሆነውን የሽቱ ቅመም ዐይነት ሁሉ፣ የከበረ ድንጋይና ወርቅ በማቅረብ በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።