ዘፍጥረት 10:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያፌት ልጆች፣ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክ እና ቲራስ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና፥ ቲራስ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። |
በሆሴዕ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም በምርኮ ወደ አሦር አፈለሳቸው። እነዚህም በአላሔ፣ ጎዛን ውስጥ በአቦር ወንዝ አጠገብ እንዲሁም በማዴ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
“በመካከላቸው ምልክት አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም የተረፉትን አንዳንዶቹን ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፣ ወደ ፉጥ፣ ወደ ታወቁት ቀስተኞች ወደ ሉድ፣ ወደ ቶቤልና ያዋን እንዲሁም ዝናዬን ወዳልሰሙትና ክብሬን ወዳላዩት ራቅ ወዳሉት ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በሕዝቦችም መካከል ክብሬን ይናገራሉ።
ዌንዳንና ያዋን ከኦሴል መጥተው ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር፤ ቀልጦ የተሠራ ብረትን፣ ብርጕድንና ከሙንን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
የመርከቦችሽ ሸራ ጥልፍ ሥራ ያለበት የግብጽ በፍታ ነበረ፤ ይህም እንደ ዐርማ አገለገለሽ። መጋረጃዎችሽ ከኤሊሳ ጠረፍ የመጡ፣ ባለሰማያዊና ሐምራዊ ቀለም ነበሩ።
“ሜሼኽና ቶቤል መቃብሮቻቸው በብዙ ሰራዊታቸው መቃብር ተከብበው ይገኛሉ፤ ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ፣ በሕያዋን ምድር ሽብራቸውን ስለ ነዙ በሰይፍ ተገድለዋል።
በስተሰሜን ርቆ ከሚገኘው ቦታ ትመጣለህ፤ አንተና ከአንተም ጋራ ብዙ ሕዝቦች፣ እጅግ ታላቅ ኀያል ሰራዊትም በፈረሶች ላይ ሆናችሁ ትመጣላችሁ።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የሜሼኽና የቶቤል ዋና አለቃ ጎግ ሆይ፤ ተነሥቼብሃለሁ፤
በአራቱ የምድር ማእዘናት ያሉትን ሕዝቦች፣ ጎግንና ማጎግን እያሳተ ለጦርነት ሊያሰልፋቸው ይወጣል። ቍጥራቸው በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ነው።