La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 1:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም ለምድር አራዊት ሁሉ፣ ለሰማይ ወፎች ሁሉ፣ በምድር ላይ ለሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” እንዳለውም ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለምድርም አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸው፥” እንዲሁም ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም በምድር ላይ ለሚኖሩ እንስሶች ሁሉ፥ በሰማይ ለሚበርሩ ወፎች ሁሉ፥ በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ ለሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ፥ በአጠቃላይ የሕይወት እስትንፋስ ላለው ፍጥረት ሁሉ ምግብ እንዲሆናቸው ልምላሜ ያለውን ሣርና ቅጠል ሁሉ ሰጥቻቸዋለሁ።” እንዲሁም ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ፥ ለሰ​ማ​ይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ለም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ሁሉ ሐመ​ል​ማሉ ሁሉ መብል ይሁ​ን​ላ​ችሁ።” እን​ዲ​ሁም ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለምድርም አራዊት ሁሉ ለሰማይም ወፎች ሁሉ ሕያዉ ነፍስ ላላቸዉ ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ የሚበቅለው ሐመልማል ሁሉ መብል ይሁንላቸዉ እንዲሁም ሆነ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 1:30
11 Referencias Cruzadas  

ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።”


ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።


ጫጩቶቹ ደም ይጠጣሉ፤ እርሱም በድን ካለበት አይታጣም።”


ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም።


በየተራራው ይሰማራል፤ ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል።


“አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን ‘ብሄሞት’ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤


ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤ አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ።


ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤


ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።