ኤፌሶን 4:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በአእምሯችሁ መንፈስ እንድትታደሱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አእምሮአችሁም በመንፈስ ይታደስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልቡናችሁን ዕውቀት አድሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ |
መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድንመላለስባቸው ያዘጋጀልንን መልካም የሆኑትን ሥራዎች እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።