ኤፌሶን 1:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ፣ ለታመኑ፣ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስም ለታመኑ፥ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ታማኞች ለሆኑት፥ በኤፌሶን ለሚገኙት ቅዱሳን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ በኤፌሶን ላሉ ቅዱሳን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን፤ |
ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ ሰው እኮ በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳንህ ላይ ምን ያህል ጕዳት እንዳደረሰ ከብዙ ሰው ሰምቻለሁ፤
በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ በሮም ላላችሁ ሁሉ፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እንግዲህ በጌታ የተወደደውንና የታመነውን ልጄን ጢሞቴዎስን የላክሁላችሁ በዚህ ምክንያት ነው፤ እርሱም በየስፍራው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከማስተምረው ትምህርት ጋራ የሚስማማውን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን የሕይወት አካሄዴን ያሳስባችኋል።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤ በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤
ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድንመላለስባቸው ያዘጋጀልንን መልካም የሆኑትን ሥራዎች እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከርሱ ጋራ ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ዐብረው ድል ይነሣሉ።”
ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ። እነሆ፤ ዲያብሎስ ሊፈትናችሁ አንዳንዶቻችሁን ወደ እስር ቤት ይጥላል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
የሰይጣን ዙፋን ባለበት እንደምትኖር ዐውቃለሁ፤ ሆኖም ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ የተገደለው ታማኙ ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።