አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው።
መክብብ 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢባን ልብ በሐዘን ቤት ነው፤ የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፥ የአላዋቂዎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁልጊዜ ስለ አስደሳች ነገር ብቻ የሚያስብ ሰው ሞኝ ነው፤ ብልኅ ግን የሞትንም ነገር ያስባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፥ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። |
አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው።
ጕረሯቸው በደረቀ ጊዜ ድግስ አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋቸውና በሣቅ እየፈነደቁ፣ ለዘላለም ላይነቁ ይተኛሉ።” ይላል እግዚአብሔር።
ባለሥልጣኖቿንና ጥበበኞቿን፣ ገዦቿንና መኳንንቷን፣ ጦረኞቿንም አሰክራለሁ፤ ለዘላለም ይተኛሉ፤ አይነቁምም፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ።
አቢግያም ወደ ናባል በተመለሰች ጊዜ፣ እነሆ፤ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ትልቅ ግብዣ አድርጎ አገኘችው፤ ክፉኛም ሰክሮ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር። ስለዚህ እስኪነጋ ድረስ ምንም አልነገረችውም።
ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፣ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፣ ይጠጡና ይዘፍኑ፣ ይጨፍሩም ነበር።