“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንድሠራለት አዝዞኛል፤ ከሕዝቡ መካከል በእናንተ ዘንድ የሚገኝ ማንኛውም ሰው፣ እግዚአብሔር አምላኩ ከርሱ ጋራ ይሁን፤ እርሱም ወደዚያው ይውጣ።’ ”
ዳንኤል 5:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ፋሬስ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፋርስ ‘መንግሥትህ ተከፍሎ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ’ ማለት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፋሬስ ማለት፥ መንግሥትህ ተከፈለ፥ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው። |
“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ “ ‘የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንድሠራለት አዝዞኛል፤ ከሕዝቡ መካከል በእናንተ ዘንድ የሚገኝ ማንኛውም ሰው፣ እግዚአብሔር አምላኩ ከርሱ ጋራ ይሁን፤ እርሱም ወደዚያው ይውጣ።’ ”
የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል። ኤላም ሆይ፤ ተነሺ፤ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢ፤ እርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ።
ጥፋት ይመጣብሻል፤ ነገር ግን በአስማትሽ እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ወጆ ከፍለሽ ለማስወገድ የማትችዪው፣ ጕዳት ይወድቅብሻል፤ ያላሰብሽው አደጋ፣ ድንገት ይደርስብሻል።