እርስ በርሳቸውም፣ “ኑና የወይን ጠጅ እንገባበዝ፤ እስክንሰክር እንጠጣ፤ ነገም ያው እንደ ዛሬ፣ ምናልባትም የተሻለ ቀን ይሆንልናል” ይባባላሉ።
ዳንኤል 4:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደልቶኝ በቤተ መንግሥቴም ተመችቶኝ እኖር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ናቡከደነፆር በቤተ መንግሥቴ በብልጽግናና በምቾት እኖር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደስ ብሎኝ በአዳራሼም ተመችቶኝ ነበር። |
እርስ በርሳቸውም፣ “ኑና የወይን ጠጅ እንገባበዝ፤ እስክንሰክር እንጠጣ፤ ነገም ያው እንደ ዛሬ፣ ምናልባትም የተሻለ ቀን ይሆንልናል” ይባባላሉ።
“ሞዓብ በአንቡላው ላይ እንዳረፈ የወይን ጠጅ፣ ከልጅነት ጀምሮ የተረጋጋ ነበረ፤ ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ በምርኮም አልተወሰደም፤ ቃናው እንዳለ ነው፤ መዐዛውም አልተለወጠም።
በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሣም፣ ጥበብህን አረከስህ። ስለዚህ ወደ ምድር ወረወርሁህ፤ ለነገሥታት ትዕይንት አደረግሁህ።
እንዲህም ብለህ ተናገረው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። “ ‘በወንዞችህ መካከል የምትተኛ አንተ ታላቅ አውሬ፣ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ። “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ” ትላለህ።
ከዚያም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በጣም ታወከ፤ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም፣ “ብልጣሶር ሆይ፤ ሕልሙም ሆነ ትርጕሙ አያስደንግጥህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ሕልሙ ለሚጠሉህ ይሁን፤ ትርጕሙም ለጠላቶችህ!
በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ተንደላቅቀው የሚኖሩትን፣ በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣ ‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።