ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው።
ዳንኤል 3:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆርም እንዲህ አላቸው፤ “ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ሆይ፤ እኔ ላቆምሁት ምስል አለመስገዳችሁ፣ አማልክቴንም አለማገልገላችሁ እውነት ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆርም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ! አማልክቴን አለማምለካችሁና ላቆምኩትም የወርቅ ምስል አለመስገዳችሁ እርግጥ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናቡከደነፆርም፦ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ፥ አምላኬን አለማምለካችሁ፥ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? |
ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው።
“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’