ቈላስይስ 4:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብሮኝ የታሰረው አርስጥሮኮስና የበርናባስ የአክስቱ ልጅ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ መመሪያ ደርሷችኋል፤ እንግዲህ ወደ እናንተ ሲመጣ ተቀበሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት፤” የሚል ትእዛዝ የተቀበላችሁለት የበርናባስ የወንድሙ ልጅ ማርቆስ እንዳረገው እንዲሁ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኔ ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ “ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ እንድትቀበሉት” ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጐቱ ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ ጋር የተማረከው አርስጥሮኮስ፥ ወደ እናንተ በሚመጣ ጊዜ ትቀበሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘዝኋችሁ የበርናባስ የአባቱ ወንድም ልጅ ማርቆስም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተገረዙት ወገን ያሉት፥ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ የበርናባስም የወንድሙ ልጅ ማርቆስ ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ፦ ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት የሚል ትእዛዝ ተቀበላችሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፥ እኔንም አጽናንተውኛል። |
ወዲያውም በከተማው ሁሉ ሁከት ተነሣ፤ ሕዝቡም አንድ ላይ በማበር የመቄዶንያ ተወላጅ የሆኑትንና ከጳውሎስ ጋራ ይጓዙ የነበሩትን ጓደኞቹን፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ይዘው ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ እየሮጡ ገቡ።
የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሱሲጴጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ እንዲሁም ጢሞቴዎስ ዐብረውት ሄዱ።
ከአድራሚጢስ ተነሥቶ በእስያ አውራጃ ባሕር ዳርቻ ላይ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው መርከብ ተሳፍረን የባሕር ጕዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ ይኖር የነበረው የመቄዶንያ ሰው፣ አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋራ ነበረ።
ለቅዱሳን ተገቢ በሆነው አቀባበል በጌታ እንድትቀበሏትና ከእናንተም የምትፈልገውን ማንኛውንም ርዳታ እንድታደርጉላት አሳስባችኋለሁ፤ ለብዙ ሰዎችና ለእኔም ጭምር ታላቅ ድጋፍ ነበረችና።
ከእኔ ጋራ ታስረው ለነበሩት ዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በሐዋርያት መካከል ስመጥሮችና በክርስቶስ በማመንም እኔን የቀደሙ ናቸው።