ምንም እንኳ ባቢሎናውያን ከተማዪቱን እንደ ከበቧት ቢሆንም የከተማዪቱ ቅጥር ተጣሰ፤ ሰራዊቱም ሁሉ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ባሉት በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በዓረባ በር ዐልፎ በሌሊት ሸሸ፤ ሽሽቱም ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር።
አሞጽ 4:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያ ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዳችሁ እፊታችሁ ባለ በተነደለ ስፍራ በኩል ትወጣላችሁ፤ ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፥” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዳችሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው መሹለኪያ ቀዳዳ ተጐትታችሁ በመውጣት ወደ ሃርሞን ትጣላላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዕራቁታችሁን ያወጡአችኋል፤ እርስ በርሳችሁም ትተያያላችሁ፤ በሬማንም ተራራ ትጣላላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያንዳንዳችሁ በየፊታችሁ በተነደለ ስፍራ ትወጣላችሁ፥ በሬማንም ትጣላላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ምንም እንኳ ባቢሎናውያን ከተማዪቱን እንደ ከበቧት ቢሆንም የከተማዪቱ ቅጥር ተጣሰ፤ ሰራዊቱም ሁሉ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ባሉት በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በዓረባ በር ዐልፎ በሌሊት ሸሸ፤ ሽሽቱም ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር።
እነርሱም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ተከተሏቸው። ሶርያውያን በጥድፊያ ሲሸሹ፣ የጣሉትንም ልብስና ዕቃ በየመንገዱ ላይ ተበታትኖ አገኙ፤ መልእክተኞቹም ተመልሰው ይህንኑ ለንጉሡ ነገሩት።
የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።
“በመካከላቸው ያለው መስፍን በምሽት ጓዙን በትከሻው ተሸክሞ ይወጣል፤ ሾልኮ እንዲሄድ ግንቡ ይነደልለታል፤ ምድሪቱንም እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።
በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።” መላዪቱ ምድር፣ በቅናቱ ትበላለች፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።