La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 9:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ ከሳኦል ቤት ሲባ የሚባል አንድ አገልጋይ ስለ ነበር፣ ወደ ዳዊት እንዲሄድ ነገሩት። ንጉሡም፣ “ሲባ የምትባለው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ጊዜ ከሳኦል ቤት ጺባ የሚባል አንድ አገልጋይ ስለ ነበር ወደ ዳዊት ጠሩት። ንጉሡም፥ “ጺባ የምትባለው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “አዎን እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሳኦል ቤተሰብ ጺባ የሚባል አንድ አገልጋይ ነበረ፤ እርሱም ወደ ዳዊት እንዲሄድ ተነገረው፤ ዳዊትም “አንተ ጺባ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሳ​ኦ​ልም ቤት አንድ ብላ​ቴና ነበረ፤ ስሙም ሲባ ነበረ፤ ወደ ዳዊ​ትም ጠሩት፤ ንጉ​ሡም፥ “አንተ ሲባ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሳኦልም ቤት ሲባ የሚባል አንድ ባሪያ ነበረ፥ ወደ ዳዊትም ጠሩት፥ ንጉሡም፦ አንተ ሲባ ነህን? አለው። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ነኝ አለ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 9:2
7 Referencias Cruzadas  

አብርሃም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ፣ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አረጋዊ አገልጋዩን እንዲህ አለው፤ “እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤


ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፤ የቀረበለትንም ከመመገብ በቀር፣ ማንኛውንም ጕዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ መልካም ነበር፤


ከርሱም ጋራ አንድ ሺሕ ብንያማውያን፣ እንዲሁም የሳኦል ቤተ ሰብ አገልጋይ ሲባ ከዐሥራ ዐምስት ወንዶች ልጆቹና ከሃያ አሽከሮቹ ጋራ ሆኖ ዐብረውት ነበሩ። ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት ወደ ዮርዳኖስ በጥድፊያ ወረዱ።


የንጉሡን ቤተ ሰው ለማምጣትና እርሱ የሚፈልገውንም ሁሉ ለማድረግ በመልካው ተሻገሩ። የጌራ ልጅ ሳሚ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ በንጉሡም ፊት ተደፍቶ፣