2 ሳሙኤል 6:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት እንደ ገና ከእስራኤል የተመረጡ በአጠቃላይ ሠላሳ ሺሕ ሰዎች ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት እንደገና ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች ሰበሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት እንደገና ከመላው እስራኤል የተመረጡ በድምሩ ሠላሳ ሺህ የሚሆኑ ምርጥ ወታደሮች በአንድነት አሰባሰበ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ደግሞ ከእስራኤል የተመረጡትን ሰባ ሺህ ያህል ሰው ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ዳግም ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ያህል ሰው ሰበሰበ። |
ከዚያም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የእስራኤልን ነገድ አለቆችና የእስራኤልን ጐሣዎች ሹማምት ሁሉ፣ ንጉሡ ሰሎሞን ወዳለበት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ከቂርያትይዓይሪም ለማምጣት ከግብጽ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ለቦ ሐማት ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ።