2 ሳሙኤል 3:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ብዙ ጊዜ ቈየ፤ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ፣ የሳኦል ቤት ግን እየተዳከመ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቈየ፤ ሆኖም ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳኦል ቤተሰብ እየተዳከመ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለብዙ ጊዜ ጦርነት ሆነ፤ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ብዙ ዘመን ጦርነት ሆነ፥ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ። |
ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የበኵር ልጁ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም፣ ሁለተኛው ዳንኤል፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ፣
ሐማም የደረሰበትን ሁሉ ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ነገራቸው። አማካሪዎቹና ሚስቱ ዞሳራም፣ “በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ዘሩ ከአይሁድ ወገን ከሆነ፣ ልትቋቋመው አትችልም፤ ያለ ጥርጥር ትጠፋለህ” አሉት።
ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋራ ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋራ ነው።
እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ነጭ ፈረስ ቆሞ ነበር፤ ተቀምጦበት የነበረውም ቀስት ይዞ ነበር፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እርሱም እንደ ድል አድራጊ ድል ለመንሣት ወጣ።