2 ሳሙኤል 23:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ይህ ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሴብ በሴትቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሼብ ባሼቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፥ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው በአንዴ የገደለ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝነኞች የሆኑት የዳዊት ወታደሮች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደ ተመለከተው ነው፤ የመጀመሪያው የታሕክሞን ተወላጅ ዮሼብ ባሼቤት የተባለው ሲሆን እርሱም ከሦስቱ ኀያላን ብልጫ ያለው ተቀዳሚ ነው፤ ይህ ሰው በአንድ ውጊያ ላይ ጦሩን አንሥቶ ስምንት መቶ ኀያላን ሰዎችን ገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊት ኀያላን ስም ይህ ነው። የሦስተኛው ክፍል አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፤ ጎራዴውን መዝዞ ስምንት መቶ ያህል ጭፍሮችን በአንድ ጊዜ የገደለ አሶናዊው አዲኖን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊት ኃያላን ስም ይህ ነው። የአለቆች አለቃ የሆነ ከነዓናዊው ኢያቡስቴ ነበረ፥ እርሱም ጦሩን አንሥቶ ስምንት መቶ ያህል በአንድ ጊዜ ገደለ። |
የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።