2 ሳሙኤል 23:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ። በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሒታዊው ኦርዮ፤ በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኬጤያዊው ኦርዮ፤ ሁሉም በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው። |
ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለልኸው ስለ ምንድን ነው? ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው።
ዳዊት በኬጢያዊው በኦርዮ ላይ ካደረሰው በደል በቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ፈቀቅ ያለበት ጊዜ አልነበረም።
ዳዊትም ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የጽሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፣ “ወደ ሳኦል ሰፈር ዐብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፣ “እኔ ዐብሬህ እወርዳለሁ” አለ።