La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 23:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዮዳሄ ልጅ የበናያስ ጀብዱ እንደዚህ ያለ ነበረ፤ እርሱም እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዮዳሄ ልጅ በናያ ያደረገው ይህ ነው፥ ስሙም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተጠርቶ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንግዲህ እንደ ሦስቱ ኀያላን ዝነኛ የሆነው በናያ የፈጸማቸው የጀግንነት ሥራዎች እነዚህ ናቸው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ያደ​ረ​ገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ኀያ​ላን ተጠ​ርቶ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዮዳሄ ልጅ በናያስ ያደረገው ይህ ነው፥ ስሙም እንደ ሦስቱ ኃያላን ተጠርቶ ነበር።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 23:22
5 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ የኢዮአብ ሰዎች፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ በአቢሳ አዛዥነት ወጡ፤ ከኢየሩሳሌም የወጡትም የቢክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ነበር።


የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ እርሱም ሁለት በጣም የታወቁ የሞዓብ ሰዎችን ገደለ፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጕድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሏል፤


ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብጻዊ ገድሏል፤ ግብጻዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም፣ በናያስ ግን ሊገጥመው በትር ይዞ ወደ እርሱ ሄደ፤ ከግብጻዊውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።


ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው።


የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ።