2 ሳሙኤል 22:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞት ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሲኦል ጣር ከበበኝ፥ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ። |
እንዲህም አለ፤ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከመቃብሩም ጥልቅ ርዳታን ፈልጌ ተጣራሁ፤ አንተም ጩኸቴን ሰማህ።