2 ሳሙኤል 22:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞት ሞገድ ከበበኝ፤ የጥፋትም ጐርፍ አጥለቀለቀኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤ የዐመፅ ጎርፍም አስፈራኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፥ |
በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም ይፈራሉ፤ በፀሓይ መውጫ ያሉት ለክብሩ ይገዛሉ፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ተቋተ፣ እንደ ተከማቸም ጐርፍ ይመጣልና።
ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “ና፤ በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ፍርድ አሳይሃለሁ።