La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 22:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ ሆነህ ትታያለህ፥ ለጠማማ ሰው ግን ጠማማ ሆነህ ትታያለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከተ​መ​ረ​ጠም ጋር የተ​መ​ረጠ ትሆ​ና​ለህ፤ ከጠ​ማማ ጋርም ጠማማ ትሆ​ና​ለህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 22:27
9 Referencias Cruzadas  

ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን፣ እግዚአብሔር ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ያስወግዳቸዋል። በእስራኤል ላይ ሰላም ይውረድ።


ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።


እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ በላይ ኀያል እንደ ሆነ አሁን ዐወቅሁ፤ እስራኤልን በትዕቢት ይዘው በነበሩት ሁሉ ላይ ይህን አድርጓልና።”


“ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋራ ክርክር ለሚገጥም ወዮለት! ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?


ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።


ከዚህም በላይ በሐሳባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ አይጠቅምም በማለታቸው፣ መደረግ የማይገባውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።


በርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።