2 ሳሙኤል 22:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ጌታ ግን ደገፈኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደጋፊዬ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ። |
ነገር ግን ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤ በድናቸውም ይነሣል። እናንተ በዐፈር ውስጥ የምትኖሩ፣ ተነሡ፤ በደስታም ዘምሩ። ጠልህ እንደ ንጋት ጠል ነው፤ ምድር ሙታንን ትወልዳለች።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ ማን ነው? ያ ሰው በጨለማ የሚሄድ ከሆነና፣ ብርሃንም ከሌለው፣ በእግዚአብሔር ስም ይታመን፤ በአምላኩም ይደገፍ።