2 ሳሙኤል 22:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍላጻውን ሰደደ፤ በተናቸውም፤ በመብረቁም ብልጭታ አወካቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻውን ከቀስቱ አስፈነጠረ፤ ጠላቶቹንም በተናቸው፤ በመብረቁም ብልጭታ አሳደዳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍላጻውን ላከ፤ በተናቸውም፤ መብረቅንም አሰምቶ አስደነገጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍላጻውን ላከ፥ በተናቸውም፥ መብረቆችን ላከ፥ አወካቸውም። |
እግዚአብሔርም የአሞራውያንን ነገሥታት በእስራኤል ፊት አሸበራቸው፤ በገባዖን እጅግ መታቸው፤ ወደ ቤትሖሮን በሚያስወጣውም መንገድ ሽቅብ ተከተላቸው፤ እስከ ዓዜቅና እስከ መቄዳም ድረስ አሳድዶ መታቸው።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ይሁን እንጂ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ ስላንጐዳጐደባቸው እጅግ ተሸበሩ፤ ድልም ተመተው ከእስራኤላውያን ፊት ሸሹ።