2 ሳሙኤል 22:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጨለማው በዙሪያው እንዲከብበው፣ ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለንተናውን በጨለማ ሰወረ፥ በውሃ በተሞላ ጥቅጥቅ ደመና፥ ራሱን ከበበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለንተናውን በጨለማ ሸፈነ። በውሃ የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ከቦታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሰወርያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን የውኃ ጨለማ አደረገ፤ በደመናም አገዘፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሰወርያውን ጨለማ፥ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን፥ በደመና ውስጥ የነበረ የጨለማ ውኃ አደረገ። |
ቤን ሃዳድ ይህን መልእክት የሰማው ዐብረውት የነበሩት ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው በሚጠጡበት ጊዜ ነበር፤ ቤን ሃዳድ ሰዎቹን፣ “በሉ ለጦርነት ተዘጋጁ” አላቸው፤ ስለዚህ ከተማዪቱን ለመውጋት ተዘጋጁ።