2 ሳሙኤል 18:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያ ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውጊያው በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ፤ በዚያን ቀን ሰይፍ ከጨረሰው ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረው ሰው በለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጦርነቱም በየገጠሩ ስለ ተስፋፋ በጦርነት ከሞቱት ሰዎች ይልቅ በደን ውስጥ ያለቁት ቊጥራቸው በዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ጦሩ በሀገሩ ሁሉ ፊት ተበተነ፤ በዚያም ቀን በሰይፍ ከተገደሉት ሕዝብ ይልቅ በበረሓ የሞቱ ይበዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ሰልፉ በአገሩ ሁሉ ፊት ላይ ተበተነ፥ በዚያም ቀን ሰይፍ ከዋጠው ሕዝብ ይልቅ ዱር ብዙ ዋጠ። |
በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋራ ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፣ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ወርካ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፣ የአቤሴሎም ራስ በዛፉ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፣ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ።
የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።
ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ።