ንጉሡም፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አኪማአስም፣ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም ባሪያህን ሊልክ ሲል፣ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።
2 ሳሙኤል 18:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ዕልፍ በልና ቁም” አለው፤ ስለዚህ ዕልፍ ብሎ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “እልፍ በልና ቁም” አለው፤ ስለዚህ እልፍ ብሎ ቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “እልፍ ብለህ ቁም” አለው። እርሱም እልፍ ብሎ ቆመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ፈቀቅ ብለህ ቁም” አለ፤ እርሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ፈቀቅ ብለህ ቁም አለ፥ እርሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ። |
ንጉሡም፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አኪማአስም፣ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም ባሪያህን ሊልክ ሲል፣ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።