ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ።
2 ሳሙኤል 18:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂውም ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው። ንጉሡም፣ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂው ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም፥ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም ድምፁንም በማሰማት ያየውን ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ፤ ያም ሯጭ ሰው እየቀረበ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም ለንጉሡ ሊነግረው ጮኸ። ንጉሡም፥ “ብቻውን እንደ ሆነ በአፉ ወሬ ይኖራል” አለ። እርሱም ፈጥኖ ቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘበኛውም ለንጉሡ ሊነግረው ጮኸ። ንጉሡም፦ ብቻውን እንደሆነ በአፉ ወሬ ይኖራል አለ። |
ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ።
ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አይቶ፣ ዘበኛውን ተጣራና፣ “እነሆ ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለ። ንጉሡም፣ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ።