2 ሳሙኤል 18:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪማአስም፣ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፣ “እንግዲያውማ ሩጥ!” አለው። ከዚያም አኪማአስ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሒማዓጽም እንደገና “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ እኔ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ኢዮአብም “እንግዲያውስ ሂድ” አለው፤ ስለዚህም አሒማዓጽ በዮርዳኖስ ሸለቆ በሚያመራው መንገድ ሲሮጥ ሄዶ ወዲያውኑ ኢትዮጵያዊውን ቀደመው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል?” አለ። እርሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪማሖስም በሰርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲንም ቀደመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል? አለ። እርሱም፦ ሩጥ አለው። አኪማአስም በሜዳው መንገድ በኩል ሮጠ፥ ኵሲንም ቀደመው። |
የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደ ገና ኢዮአብን፣ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፣ “ልጄ ሆይ፣ መሄድ ለምን አስፈለገህ? ሽልማት የሚያሰጥህ ምን የምሥራች ይዘህ ነው?” ብሎ መለሰለት።
ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ።