2 ሳሙኤል 18:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ቀንደ መለከት ነፍቶ ስለ ከለከላቸው፣ ሰራዊቱ እስራኤልን ማሳደዱን አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም ቀንደ መለከት ነፋ፤ ሠራዊቱ እስራኤልን እንዳያሳድዱም ስለከለከለ ከማሳደድ ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ ጦርነቱ ይቆም ዘንድ እምቢልታ እንዲነፉ አዘዘ፤ ወታደሮቹም እስራኤላውያንን ከማሳደድ ተመልሰው መጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ሕዝቡን ስለ ራራላቸው መለከት አስነፋ፤ ሕዝቡም እስራኤልን ተከትለው እንዳያሳድዱአቸው መለሳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ሕዝቡን ከልክሎ ነበርና ቀንደ መለከት ነፋ፥ ሕዝቡም እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ። |
ከዚህም በኋላ ሴቲቱ ብልኅነት የተሞላበት ምክሯን ይዛ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቈርጠው ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ ስለዚህ ኢዮአብ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ከከተማዪቱ ርቀው በየአቅጣጫው ተበታተኑ፤ እያንዳንዳቸውም ወደ የቤታቸው ሄዱ፤ ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።