2 ሳሙኤል 16:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡ ወታደሮችና የክብር ዘቦቹ ሁሉ በዳዊት ግራና ቀኝ ቢኖሩም እንኳ፣ በዳዊትና በሹማምቱ ላይ ሁሉ ድንጋይ ይወረውርባቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ቢኖሩም እንኳ፥ ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሥ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በሠራዊቱና በክብር ዘበኞቹ መካከል እያለ ሺምዒ በዳዊትና በመኳንንቱ ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ባሪያዎች ድንጋይ ይወረውር ነበር፥ በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኃያላኑ ሁሉ ነበሩ። |
እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ በደሌን አይቍጠርብኝ፤ ንጉሥ ጌታዬ ከኢየሩሳሌም በወጣህባት ዕለት የፈጸምሁትን ስሕተት እርሳው፤ ከአእምሮህም አውጣው።