እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
2 ሳሙኤል 16:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ለአቤሴሎም በሰገነቱ ላይ ድንኳን ተከሉለት፤ እዚያም መላው እስራኤል እያየው ከአባቱ ቁባቶች ጋራ ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለአቤሴሎም በሰገነቱ ላይ ድንኳን ተከሉለት፤ እዚያም መላው እስራኤል እያየው ከአባቱ ዕቁባቶች ጋር ተኛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በቤተ መንግሥቱ ጣራ ላይ ለአቤሴሎም ድንኳን ተከሉለት፤ ሰውም ሁሉ እየተመለከተው ወደ ድንኳኑ ገብቶ ከአባቱ ቊባቶች ጋር ተገናኘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአቤሴሎምም በሰገነት ላይ ድንኳን ተከሉለት፤ አቤሴሎምም በእስራኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባቶች ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአቤሴሎምም በሰገነት ላይ ድንኳን ተከሉለት፥ አቤሴሎምም በእስራኤል ሁሉ ፊት ወደ አባቱ ቁባቶች ገባ። |
እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
አንድ ቀን ማታ፣ ዳዊት ከዐልጋው ተነሥቶ በንጉሥ ቤት ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፣ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች።
ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ ንጉሡም ቤቱን እንዲጠብቁ ትቷቸው የሄደውን ዐሥሩን ቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከ ሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፣ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ።
ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በሚቀጡ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
ከዚህ በኋላ ሙሴና መላው የእስራኤል ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ እያለቀሱ ሳለ፣ አንድ እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተ ሰቡ መጣ።