በዚህ ጊዜ ዮናታንና አኪማአስ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዓይንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፣ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።
2 ሳሙኤል 15:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱ ሳዶቅና አብያታር እዚያው ከአንተው ጋራ ይሆኑ የለምን? ከንጉሡ ቤትም የምትሰማትን ሁሉ ንገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱ ሳዶቅና አብያታር በዚያ ከአንተው ጋር አይደሉምን? ስለዚህ ከቤተ መንግሥቱ የምትሰማትን ሁሉ ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያው ይገኛሉ፤ በቤተ መንግሥት የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለእነርሱ ትነግራቸዋለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያ ከአንተ ጋር ናቸው። ከንጉሡ ቤትም የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያ ከአንተ ጋር አይደሉምን? ከንጉሡ ቤትም የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው። |
በዚህ ጊዜ ዮናታንና አኪማአስ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዓይንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፣ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።