2 ሳሙኤል 13:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም ፈጥኖ ሸሸ። ለዘብ ጥበቃ የቆመውም ሰው ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ከርሱ በስተ ምዕራብ ካለው መንገድ ብዙ ሰዎች በተራራው ጥግ ቍልቍል ሲወርዱ አየ፤ ዘብ ጠባቂውም ሄዶ ለንጉሡ፣ “ከበስተ ሖሮናይም አቅጣጫ በኰረብታው ጥግ ላይ ሰዎች ቍልቍል ሲወርዱ አያለሁ” ብሎ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎምም ፈጥኖ ሸሸ። ለዘብ ጥበቃ የቆመውም ሰው ቀና ብሎ ተመለከተ፤ እነሆም፥ በኋላው ብዙ ሰዎች በተራራው ጥግ ሲመጡ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ አቤሴሎም ሸሽቶ አምልጦ ነበር፤ ለዘብ ጥበቃ ተረኛ የነበረውም ወታደር ልክ በዚያን ሰዓት ከሖርናይም ወደዚህ በሚመጣው መንገድ ላይ ካለው ኮረብታ ብዙ ሕዝብ ወደ ታች ሲወርድ አየ፤ ወደ ንጉሡም ቀርቦ ያየውን ሁሉ ተናገረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም ኮበለለ። ጕበኛውም ጕልማሳ ዓይኑን ከፍ አደረገ፥ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። |
ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ።
ይህ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ፣ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ ወደ ቤቱም ገብቶ፣ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያሳርፍ፣ እባብ እንደሚነድፈው ነው።