2 ሳሙኤል 13:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን ሊሰማት አልፈለገም፤ ከርሷ ይልቅ ብርቱ ስለ ነበር፣ በግድ አስነወራት፤ ከርሷም ጋራ ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን ሊሰማት አልፈለገም፤ ከእርሷ ይልቅ ብርቱ ስለ ነበር፥ በግድ አስገድዶ ደፈራት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን ሊያዳምጣት አልፈቀደም፤ እርሱም ከእርስዋ ይልቅ ብርቱ ስለ ነበረ በኀይል አስገድዶ ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምኖንም ቃልዋን አልሰማም፤ ይዞም አደከማት፤ ከእርስዋም ጋር ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃልዋን ግን አልሰማም፥ ከእርስዋ ይልቅ ብርቱ ነበረና በግድ አስነወራት፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ። |
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋራ ይተኛል።
ንጉሡ ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ሲመለስ አስቴር ደገፍ ባለችበት ድንክ ዐልጋ ላይ ሐማ ተደፍቶ ነበር። ንጉሡም፣ “ይባስ ብሎ ዐብራኝ ያለችውን ንግሥት በገዛ ቤቴ ሊደፍራት ያስባልን?” ሲል ተናገረ። ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ ገና እንደ ወጣ፣ የሐማን ፊት ሸፈኑት።
“ ‘ከእኅትህ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፣ ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋራ በግብረ ሥጋ አትገናኝ።