የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”
2 ሳሙኤል 11:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ሄደ፤ እዚያ እንደ ደረሰም፣ ከኢዮአብ የተቀበለውን መልእክት በሙሉ ለዳዊት ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ሄደ፤ እዚያ እንደደረሰም ከኢዮአብ የተቀበለውን መልእክት በሙሉ ለዳዊት ነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም መልእክተኛው ወደ ዳዊት ሄዶ ኢዮአብ ያዘዘውን ሁሉ እንዲህ ሲል ነገረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮአብም መልእክተኛ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደርሶም ኢዮአብ የነገረውን የጦርነቱን ዜና ሁሉ ለዳዊት ነገረው። ዳዊትም በኢዮአብ ላይ ተቈጣ። ያንም መልእክተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተማዋ ቅጥር ለምን ቀረባችሁ? በቅጥሩም እንደምትቈስሉ አታውቁምን? የይሩበዓል ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? አንዲት ሴት ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላበት በቴቤስ የሞተ አይደለምን? ስለምን ወደ ቅጥሩ ቀረባችሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልእክተኛውም ተነሥቶ ሄደ፥ ኢዮአብም ያዘዘውን ሁሉ ለዳዊት ነገረው። |
የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”
መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ ዐየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳድደን መለስናቸው።