አሞናውያን፣ ዳዊት እንደ ጠላቸው ባወቁ ጊዜ፣ ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺሕ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥ ከአንድ ሺሕ ሰዎቹ ጋራ ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰዎች ቀጠሩ።
2 ሳሙኤል 10:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የሱባና የረአብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የጾባና የረሖብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሞናውያን ተሰልፈው ወጥተው የእነርሱ ዋና ከተማቸው በሆነችው በራባ መግቢያ በር አጠገብ ስፍራቸውን ያዙ፤ ሌሎቹ ሶርያውያን፥ ከጦብና ከማዕካ የመጡት ጦረኞች በአንድ ሜዳማ ቦታ ስፍራቸውን ያዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱባና የሮዖብ ሶርያውያን፥ የአስጦብና የአማሌቅም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ተሰለፉ፥ የሱባና የረአብ ሶርያውያን፥ የጦብና የመዓካም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ። |
አሞናውያን፣ ዳዊት እንደ ጠላቸው ባወቁ ጊዜ፣ ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺሕ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥ ከአንድ ሺሕ ሰዎቹ ጋራ ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሰዎች ቀጠሩ።
ዳዊት የሱባን ኀይል በደመሰሰ ጊዜ፣ ሬዞን ሰዎቹን በዙሪያው አሰባስቦ የወንበዴ አለቃ ሆነ፤ ሰዎቹም ወደ ደማስቆ ሄደው ተቀመጡ፤ በዚያም አነገሡት።
ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤ እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣ አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።
ወደ ምጽጳ፣ ጎዶልያስ ዘንድ መጡ፤ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፣ የተንሑሜት ልጅ ሠራያ፤ የነጦፋዊው የዮፌ ልጆች፣ የማዕካታዊ ልጅ ያእዛንያን ሰዎቻቸውም ነበሩ።