2 ሳሙኤል 1:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊትና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ተከታዮቹ ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው ቀደዱ። |
ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና ዐብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀድዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ራሱ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን አጀበ።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ወዲያው እንዳነበበ ልብሱን ቀድዶ፣ “ከቈዳ በሽታው እንድፈውሰው ይህን ሰው ወደ እኔ መላኩ እኔ ገድዬ ማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነውን? እንግዲህ ጠብ ሲፈልገኝ እዩ!” አለ።
‘በዚህ ስፍራና በሕዝቡ ላይ የተናገረውን በሰማህ ጊዜ፣ ልብህ ስለ ተነካና በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፣ ራስህን ዝቅ አድርገህ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ፣ እኔም ሰምቼሃለሁ ይላል እግዚአብሔር።
መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም ማቅ ለብሶ፣ በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ አምርሮ እየጮኸ ወደ ከተማዪቱ መካከል ወጣ።
ልባችሁን እንጂ፣ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ፣ ቍጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ፣ ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገሥ ነውና።
በዚህ ጊዜ ኢያሱ ልብሱን ቀደደ፤ በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት በግንባሩ ተደፋ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎችም እንደዚሁ አደረጉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።