2 ጴጥሮስ 1:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሁሉ አስቀድሞ ይህን ልታውቁ ይገባችኋል፤ በመጽሐፍ ያለው የትንቢት ቃል ሁሉ ማንም ሰው በገዛ ራሱ መንገድ የሚተረጕመው አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሁሉ አስቀድማችሁ ይህን አስተውሉ፥ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁሉ በፊት ማስተዋል የሚገባችሁ በቅዱስ መጽሐፍ የሚገኘውን ማንኛውንም ትንቢት ማንም ሰው በራሱ ግላዊ አስተሳሰብ ሊተረጒመው የማይችል መሆኑን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ |
ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቧልና።
ደግሞም ሕግ የተሰጠው ለጻድቃን ሳይሆን፣ ለሕግ ተላላፊዎችና ለዐመፀኞች፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ለሌላቸውና ለኀጢአተኞች፣ ቅድስና ለሌላቸውና እግዚአብሔርን ለሚንቁ፣ አባትና እናታቸውን ለሚገድሉ፣ ለነፍሰ ገዳዮች መሆኑን እናውቃለን፤