2 ነገሥት 5:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ወዲያው እንዳነበበ ልብሱን ቀድዶ፣ “ከቈዳ በሽታው እንድፈውሰው ይህን ሰው ወደ እኔ መላኩ እኔ ገድዬ ማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነውን? እንግዲህ ጠብ ሲፈልገኝ እዩ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቆዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቊጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቈዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለምጹ እፈውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስደዱ እኔ በውኑ ለመግደልና ለማዳን የምችል አምላክ ነኝን? ተመልከቱ፥ የጠብ ምክንያት እንደሚፈልግብኝ ተመልከቱ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ “ሰውን ከለምጹ እፈውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስደዱ እኔ በውኑ ለመግደልና ለማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነውን? ተመልከቱ፤ የጠብ ምክንያትም እንደሚፈልግብኝ እዩ፤” አለ። |
የእስራኤልም ንጉሥ የአገሩን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ፣ “ይህ ሰው እንዴት ጠብ እንደሚፈልግ ታያላችሁ፤ ሚስቶቼንና ልጆቼን፣ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው በጠየቀኝ ጊዜ አልከለከልሁትም” አላቸው።
እነሆ፤ በወጉ መሠረት ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ፣ ሹማምቱና መለከት ነፊዎቹ ከአጠገቡ ሆነው አየች። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ይፈነጥዝ፣ መለከትም ይነፋ ነበር። ጎቶልያም ልብሷን ቀድዳ፣ “ይህ ክሕደት ነው! ክሕደት ነው!” ብላ ጮኸች።
ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ እንዲሁም ታሪክ መዝጋቢው የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የጦር አዛዡ የተናገረውንም ሁሉ ነገሩት።
ለእስራኤልም ንጉሥ የያዘው ደብዳቤ፣ “ከቈዳ በሽታ እንድትፈውሰው ይህን ደብዳቤ አስይዤ አገልጋዬን ንዕማንን ወደ አንተ ልኬዋለሁ” የሚል ነው።
በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀድዶ፣ “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ተናግሯል፤ ከዚህ ሌላ ምን ምስክርነት ያስፈልገናል? በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል መናገሩን እናንተው ራሳችሁ ሰምታችኋል፤
“እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።