“የጌታችሁ ልጆች ከእናንተ ጋራ ስለ ሆኑ፣ ሠረገሎችና ፈረሶች፣ የተመሸገች ከተማና መሣሪያም ስላላችሁ፣ ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ
2 ነገሥት 5:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤልም ንጉሥ የያዘው ደብዳቤ፣ “ከቈዳ በሽታ እንድትፈውሰው ይህን ደብዳቤ አስይዤ አገልጋዬን ንዕማንን ወደ አንተ ልኬዋለሁ” የሚል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይዞት የሄደውም መልእክት “ይህ ደብዳቤ የእኔ ሠራዊት አዛዥ ስለ ሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከቆዳ በሽታ በማንጻት እንድትፈውሰው እፈልጋለሁ” የሚል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይዞት የሄደውም መልእክት “ይህ ደብዳቤ የእኔ ሠራዊት አዛዥ ስለ ሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከቈዳ በሽታ በማንጻት እንድትፈውሰው እፈልጋለሁ” የሚል ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እስራኤልም ንጉሥ፦ ደብዳቤውን አደረሰ። ደብዳቤውም እንዲህ ይላል፥ “ደብዳቤው ካንተ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ባለሟሌን ንዕማንን ወደ አንተ ልኬዋለሁና ከለምጹ ፈውሰው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም ንጉሥ “ይህች ደብዳቤ ወደ አንተ ስትደርስ ባሪያዬን ንዕማንን ከለምጹ ትፈውሰው ዘንድ እንደ ሰደድሁልህ እወቅ፤” የሚል ደብዳቤ ወሰደ። |
“የጌታችሁ ልጆች ከእናንተ ጋራ ስለ ሆኑ፣ ሠረገሎችና ፈረሶች፣ የተመሸገች ከተማና መሣሪያም ስላላችሁ፣ ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ
የሶርያም ንጉሥ፣ “በል እንግዲያው አሁኑኑ ሂድ፤ እኔም ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እጽፋለሁ” አለው፤ ስለዚህ ንዕማን ዐሥር መክሊት ብር፣ ስድስት ሺሕ ሰቅል ወርቅና ዐሥር ሙሉ ልብስ ይዞ ሄደ።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ወዲያው እንዳነበበ ልብሱን ቀድዶ፣ “ከቈዳ በሽታው እንድፈውሰው ይህን ሰው ወደ እኔ መላኩ እኔ ገድዬ ማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነውን? እንግዲህ ጠብ ሲፈልገኝ እዩ!” አለ።