2 ነገሥት 5:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንዕማንም ወደ ጌታው ሄዶ ከእስራኤል የመጣችው ልጃገረድ ያለችውን ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንዕማንም ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ልጃገረዲቱ ያለችውን ሁሉ ነገረው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንዕማንም ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ልጃገረዲቱ ያለችውን ሁሉ ነገረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስቱም ወደ እርሱ ገብታ፥ “ከእስራኤል ሀገር የመጣች ይች ብላቴና እንደዚህና እንደዚህ አለች” ብላ ነገረችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንዕማንም ገብቶ ለጌታው “ከእስራኤል አገር የሆነች አንዲት ብላቴና እንዲህና እንዲህ ብላለች፤” ብሎ ነገረው። |
የሶርያም ንጉሥ፣ “በል እንግዲያው አሁኑኑ ሂድ፤ እኔም ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እጽፋለሁ” አለው፤ ስለዚህ ንዕማን ዐሥር መክሊት ብር፣ ስድስት ሺሕ ሰቅል ወርቅና ዐሥር ሙሉ ልብስ ይዞ ሄደ።
ኢየሱስ አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን፣ “ወደ ቤትህ ሂድ፣ ለዘመዶችህም ጌታ ምን ያህል ታላቅ ነገር እንዳደረገልህና ያሳየህን ምሕረት ንገራቸው” አለው።