2 ነገሥት 4:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “ጌታዬ፤ ለመሆኑ እኔ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘አጕል ተስፋ እንዳትሰጠኝ’ አላልሁህምን?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም “ጌታዬ፥ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘የማይፈጸምስ የተስፋ ቃል አትስጠኝ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቲቱም “ጌታዬ፥ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘የማይፈጸምስ የተስፋ ቃል አትስጠኝ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “በውኑ ከጌታዬ ልጅን ለመንሁን? እኔም አታታልለኝ አላልሁህምን?” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም “በውኑ ከጌታዬ ልጅን ለመንሁን? እኔም ‘አታታልለኝ’ አላልሁህምን?” አለች። |
ኤልሳዕም፣ “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው።
ኤልሳዕም ግያዝን፣ “እንግዲህ ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬን ያዝና ሩጥ፤ መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህ መልስ አትስጥ፤ በትሬንም በልጁ ፊት ላይ አድርግ” አለው።