2 ነገሥት 4:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም ፀነሰች፤ ኤልሳዕ እንደ ነገራትም በተባለው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ሴቲቱ ፀነሰች፥ በዓመቱም ኤልሳዕ በነገራት ወራት ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ፀነሰች፤ በዚያም ወራት በአዲሱ ዓመት ኤልሳዕ እንዳላት ወንድ ልጅ ወለደች። |
ኤልሳዕም፣ “የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው።
አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረ በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ።