አገልጋዩንም፣ “ውጣና ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ተመለከተና፤ “በዚያ ምንም የለም” አለው። ኤልያስ ሰባት ጊዜ፣ “እንደ ገና ሂድ” አለው።
2 ነገሥት 4:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዩን ግያዝንም፣ “ሱነማዪቱን ጥራት” አለው፤ በጠራትም ጊዜ መጥታ በፊቱ ቆመች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግያዝ ተብሎ የሚጠራውንም አገልጋዩን፥ “ሄደህ ሱነማዊትን ጥራ” አለው፤ እርሷም መጥታ በፊቱ ቆመች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግያዝ ተብሎ የሚጠራውንም አገልጋዩን፥ “ሄደህ ሱነማዊትን ጥራ” አለው፤ እርስዋም መጥታ በፊቱ ቆመች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውንም ግያዝን፥ “ይህችን ሱማናዊት ጥራ” አለው። በጠራትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውንም ግያዝን “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው። |
አገልጋዩንም፣ “ውጣና ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ተመለከተና፤ “በዚያ ምንም የለም” አለው። ኤልያስ ሰባት ጊዜ፣ “እንደ ገና ሂድ” አለው።
ኢዮሣፍጥ ግን፣ “በርሱ አማካይነት እግዚአብሔርን ለመጠየቅ እንድንችል፣ የእግዚአብሔር ነቢይ እዚህ የለምን?” በማለት ጠየቀ። ከእስራኤል ንጉሥ የጦር አለቆችም አንዱ፣ “ቀድሞ የኤልያስን እጅ ያስታጥብ የነበረው፤ የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ በዚህ አለ” ብሎ መለሰለት።
ኤልሳዕም፣ “ ‘ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል፤ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊአለሽ? ለንጉሡ ወይስ ለሰራዊቱ አዛዥ የምንነግርልሽ ጕዳይ አለን?’ ብለህ ጠይቃት” አለው። ሴቲቱም መልሳ፣ “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” አለችው።