2 ነገሥት 18:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ እንዲህ ይላል፤ ከእጄ ሊያድናችሁ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቅያስ አትታለሉ! እርሱ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቅያስ አትታለሉ! እርሱ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ |
ደግሞም ሕዝቅያስ፣ ‘እግዚአብሔር በርግጥ ያድነናል፤ ይህች ከተማ ለአሦር ንጉሥ ዐልፋ አትሰጥም’ እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።
አሁንም ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ አያስታችሁም። የየትኛውም አገር ሕዝብ ወይም መንግሥት አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ መታደግ የቻለ ስለሌለ አትመኑት። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!”
ስለዚህ ንጉሡ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ዳንኤልን አመጡት፤ ወደ አንበሶችም ጕድጓድ ጣሉት። ንጉሡም ዳንኤልን፣ “ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ያድንህ!” አለው።
እርሱም አምላክ ከተባለና ከሚመለከው ነገር ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተቃዋሚ ነው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተቀምጦ፣ “እኔ አምላክ ነኝ” እያለ ዐዋጅ ያስነግራል።