የአሦር ንጉሥ ግን ሆሴዕ እንደ ከዳው ተገነዘበ፤ ምክንያቱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሲጎር መልክተኞች ስለ ላከና በየዓመቱም ያደርግ እንደ ነበረው ለአሦር ንጉሥ ስላልገበረ ነው፤ ከዚህም የተነሣ ስልምናሶር ይዞ ወህኒ ቤት አስገባው።
2 ነገሥት 18:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል፣ የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቆስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቈስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብፅ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል፥ ያቈስለውማል፤ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ትታመናለህ፤ ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል፤ ያቈስለውማል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።’ |
የአሦር ንጉሥ ግን ሆሴዕ እንደ ከዳው ተገነዘበ፤ ምክንያቱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሲጎር መልክተኞች ስለ ላከና በየዓመቱም ያደርግ እንደ ነበረው ለአሦር ንጉሥ ስላልገበረ ነው፤ ከዚህም የተነሣ ስልምናሶር ይዞ ወህኒ ቤት አስገባው።
“ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእኔ ያልሆነውን ሐሳብ ይከተላሉ፤ ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ በኀጢአት ላይ ኀጢአት ይጨምራሉ።
እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት! የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው።
ስለ ግብጽ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ በከርከሚሽ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ባሸነፈው በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ኒካዑ ሰራዊት ላይ የተነገረ መልእክት ይህ ነው፤
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን እንዲሁም በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤